የትራፊክ መጨናነቅ የሚስተዋልባቸው አምስት አደባባዮችን በትራፊክ መብራት እየተቀየሩ ነው፡፡

የትራፊክ መጨናነቅ የሚስተዋልባቸው አምስት አደባባዮችን በትራፊክ መብራት እየተቀየሩ ነው፡፡

ሚያዝያ 7፣ 2012፤ የትራፊክ መጨናነቅ የሚስተዋልባቸው አምስት አደባባዮችን ፈርሰው በትራፊክ መብራት መቆጣጣሪያ እየተቀየሩ መሆኑን የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውkል፡፡

በተለይ በከተማዋ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የሚስተዋሉ የትራፊክ መጨናነቅና የፍሰት ችግሮች የሚታይባቸው አራት አደባባዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሚገኝ ኤጀንሲው አስረድቷል፡፡

በመሆኑም በጎሮ፣ በጦር ሀይሎች፣ በአፍሪካ ህብረት እና በአየር ጤና አደባባዮች የማሻሻያ ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም የአንድ አደባባይ ማሻሻያ ስራ በቅረቡ ይጀመራል፡፡

የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እንደገለጸው በከተማዋ ለምስተዋሉ የትራፊክ ፍሰት እና ደህንነት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ጥናትን መሰረት ባደረገ መልኩ ወደትግበራ ተገብቷል፡፡

አደባባዮቹን በማሻሻል በትራፊክ መብራት መቆጣጣሪያ ዘዴ የመተከት ስራ መጋቢት 20 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል፡፡

ስራውን በማከናወን ላይ የሚገኘው ኃቭሪም ኮንስትራክሽን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እስከ አሁን እየተከናወነ ባለው ስራ አራቱንም አደባባዮችን በማፍራስ አፈሩን የማንሳት፣ የኮንክሪት ሙሌት፣ ለአስፋልት ስራ ዝግጅት ዲዛይን የማጣጣም ስራ በመከናወን ላይ እንደሆነም አስታውkል፡፡

ስራዎቹ በሚከናወኑበት አደባባዮቹ አካባቢ የማሻሻያ ስራውን ዓለማ እና ጥቅሞች እንዲሁም የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች በኤጀንሲው እና ስራውን በማከናወን ላይ በሚገኘው ተቋራጭ በመተላላፍ ላይ ይገኛል፡፡

ስራው አደባባዮቹ ላይ ተገቢውን ማሻሻያ በማድረግ፣ የትራፊክ መብራቶችን መትከል እና ሌሎች አስፈላጊ ማሻሻያ ስራዎችን የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡

ይህም በአካባቢዎቹ ይታዩ የነበሩ የትራፊክ መጨናነቆችን በማስቀረት ደህንነቱ የተጠበቀ ሰላማዊና የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል፡፡

ከዚህ በፊት በተጠቀሱት አደባባዮች አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ፣ ተሽከርካሪዎቹ በጣም ተጠጋግተው ከመሄዳቸው የተነሳ አነስተኛ ግጭቶች መከሰት እንዲሁም የእግረኛ መሸጋሪያ ዜብራዎች ላይ ጭምር ስለሚቆሙ እግራኞችም መንገድ ለማቋረጥ እንደሚቸገሩ ይታወቃል፡፡

አሽከርካሪዎች እነዚህን አደባባዮች አልፈው ለመሄድ ረዥም ጊዜ በሚቆሙበት ወቅት የሚባክነው ነዳጅም ቀላል የማይባል ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ወደ ግል ጉዳያቸው እና ወደስራ ቦታቸው በወቅቱ ስለማይደርሱ በግለሰብም ሆነ በሀገር ደረጃ የሚያሳድረው ኢኮኖሚያዊ ጨና ከባድ ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር የትራፊክ ፍሰቱን ለማስተናበር በርካታ የኤጀንሲው ደንብ ማስከበር ባለሙያዎች እና ትራፊክ ፖሊሶች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የተለያዩ የአየር ሁኔታ ባለበት ወቅት ጭምር በመሆኑ አድካም እንደሆነም ይታወቃል፡፡

Leave a Reply