የመንገድ ደህንትን ለማረጋገጥ ቴክኖሎጂን በተገቢው መጠቀምና ማስተግበር እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፤ 2014፤ በመዲናዋ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን በተገቢው ማስፈፀምና መጠቀም እንደሚገባ አለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ ገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከብሉምበርግ ኢኒሼቲብ የከተማዋ አጋር ከሆነው ግሎባል ሮድ ሴፍቲ ፓርትነርሺፕ ጋር በመተባበር 80 ለሚሆኑ ለህግ አስፈፃሚ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ተሰጥቷል፡፡
አቅም ማጎልበቻው በሁለት ዙር ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትና ከየክፍለ ከተማው የተውጣጡ የትራፊክ ዘርፍ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
ስልጠናው በተለይ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥ ከሚያግዙ መሰረታዊ ጉዳዮች ውስጥ የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሳሪያ እና የደህንነት ቀበቶ አጠቃቀምን የተመለከተ በንድፈ-ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ነው፡፡
በብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ የህግ ማስከበር ባለሙያ አቶ ቶሎሳ ገዳ እንደተናገሩት የፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳር እና የደህንነት ቀበቶ አጠቃቀምን ለማስተግበር የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም በህግ ማስከበሩ ረገድ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን በውጤታማነት ለመከወን ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀምና ማስተግበር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም በፍጥነት ማሽከርከር የትራፊክ ግጭት እንዲከሰት ከሚያደርጉ መንስኤዎች 50 በመቶ ይህሉ ነው ያሉት አቶ ቶሎሳ በተገቢው ህጉን በማስተግበር አደጋውን መቀነስ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
የደህንነት ቀበቶውም ቢሆን በአግባቡና በስሪት ስታንዳርዱ መሰረት መጠቀምና ህጉን ማስተግበር ከተቻለ ፊት ለፊት ለሚቀመጡ እስከ 50 በመቶ ከኋላ ለሚቀመጡ ደግሞ 25 በመቶ የአደጋውን የጉዳት መጠን መቀነስ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ለሰልጣኞቹ የሰርተፍኬት ርክክብ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡
ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011 557 32 66 ወይም 09 11 33 97 24 ወይም 09 10 53 22 73
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢሜይል፦ aagtpmo@gmail.com

Leave a Reply