የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012፣ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ለተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የመንገድ ትራፊክ አደጋው በ2011 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር መቀነሱ ተጠቁሞ የሞት አደጋን በ10ሺ ተሽከርካሪ 27 ለማድረስ ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ በመግለጫው ተነስቷል፡፡

የግንዛቤ ፈጠራና የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመላክቷል፡፡

በከፍተኛ መጠን እየጨመረ የመጣውን የተሽከርካሪ ቁጥር በአግባቡ በማስተናበር የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውkል፡፡

በመግለጫው ወቅት የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መጠን ለመቀነስ የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓት ትምህርቱ የማካተት ስራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የመንጃ ፈቃድ፣ የተሽከርካሪ ምርመራና የትራፊክ ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመንገድ ትራፊክ አደጋ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እየፈጠረ ያለውን ጫና ለመቀነስ የግንዛቤ ፈጠራዉንና የቁጥጥር ስራዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Leave a Reply