ከታለመለት የነዳጅ ድጎማ አፈፃፀም ዙሪያ ከተሽከርካሪ ባለንብረቶች ማህበር ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፤ 2014፤ በከተማዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አፈፃፀም ዙሪያ ከፀሀይ የኮድ-1 ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር ጋር በየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ውይይት ተደርጓል፡፡

መንግስት ከሚተገብራቸው ዜጋ ተኮር ስራዎች መካከል የታለመለት የነዳጅ ድጎማው በተገቢው እንዲፈፀም ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በተጓዳኙም በአንዳንድ የመረጃ አለመሟላትና አለመካተት የተነሳ በታለመለት የነዳጅ ድጎማው አፈፃፀም ላይ ክፍተት መታየቱም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ስርዓት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አልዓዛር ይርዳው እንደተናገሩት በታለመለት የነዳጅ ድጎማው መንግስት ብዙሃኑን የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚጠቀሙ የህዝረተሰብ ክፍሎችን ለመጥቀም ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድ እንደአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለታለመለት ነዳጅ ድጎማ አተገባበር እንዲመች በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተሰርተው አስፈላጊው መረጃ ለሚመለከተው ተቋም መላኩንም አስታውቀዋል፡፡

አቶ አልዓዛር አያይዘውም በግንዛቤና በመረጃ ክፍተቶች የሚስተዋሉ ችግሮች መኖራቸውን በመጥቀስ እነዚህንና መሰል ችግሮች ለመሙላት እንዲህ ዓይነት መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ ማሳደግና በጋራ ተወያይን መግባባት ላይ መድረስ አለብንም ብለዋል፡፡

አክለውም አሁን በትግበራ ወቅት እያጋጠሙ ያሉ አንዳንድ ክፍተቶችን ለማስተካከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የየካ ትራንስፖር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ጀማል እንደገለፁት  በታለመለት ነዳጅ ድጎማ አጠቃቀም ዙሪያ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን ማህበሩ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱና ከቢሮው ጋር በመሆን እየተፈቱ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም በትራንስፖር ዘርፍ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ዙሪያ በተለይ በማህበሩ ውስጥ ያሉ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ወደ መስመር ገብተው አገልግሎት የማይሰጡ ወደ መስመር ገብተው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ በውይይቱ ወቅት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

ከማህበሩ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በነዳጅ ድጎማው ዙሪያ የመረጃ ጥራት ጉድለት፣ የነዳጅ ድጎማው በተገቢው ተጠቃሚ እየሆኑ እንዳልሆኑ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ተገቢውን መረጃ እና አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተን በነዳጅ ማደያዎች ተገቢው የነዳጅ ድጎማ አገልግሎት እያገኙ እንዳልሆነና ችግሩ እንዲፈታላቸውም በውይይቱ ወቅት አንስተዋል፡፡

ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- 011 666 33 74

የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo

ኢ-ሜይል፦ aagtpmo@gmail.com

Leave a Reply