በ2012 በጀት ዓመት ከ6 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች የመንገድ ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ምርመራ መደረጉ ተገለጸ፡፡

በ2012 በጀት ዓመት ከ6 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች የመንገድ ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ምርመራ መደረጉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣2012፤ በ2012 ዓ.ም ከ6 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች የመንገድ ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ምርመራ ማድረጉን የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በበጀት ዓመቱ ለ6 ሺህ 740 ተሽከርካሪዎች የመንገድ ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ 4 ሺህ 494 ተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ምርመራውን ጉድለት ሳይገኝባቸው አልፈዋል፡፡

የድንገተኛ እና የተሽከርካሪ የተቋማት ብቃት ማረጋገጥ እና ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እንደገለጸው

የቴክኒክ ጉድለት ያለባቸውን ተሽከርካሪዎች በ5 ቀናት ውስጥ አስተካክለው እንዲመጡ ተደርጓል፡፡

የድንገተኛና የተሽከርካሪ የተቋማት ብቃት ማረጋገጥ እና ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በዘርፉ ለቴክኒክ ምርመራ ተቋማት፤ ለጋራጅ ቤቶች ፈቃድ የመስጠትና የማደስ እንዲሁም ተቋማቱን የመከታተልና የመቆጣጠር ስራዎችን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አከናውኗል፡፡

በነዚህም በተሰጡ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ዳይሬክቶሬቱ አሳውቋል፡፡

Leave a Reply