በግብዓት እጥረት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የተሸከርካሪ ሠሌዳ ከነገ ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፤ 2014፤ በመዲናዋ የኮድ-02 ተሸከርካሪዎች ሰሌዳ በግብዓት እጥረት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት ከነገ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ፤ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የኮድ02አ.አ ሰሌዳ በግብዓት እጥረት ምክንያት አትሞ እያስረከበ ስላልሆነ የሰሌዳ እጥረት ያጋጠመ መሆኑን ግንቦት 06 ቀን 2014 ዓ.ም ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡

የነበረው የሠሌዳ ምርት እጥረት የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ችግሩን እየፈታዉ በመሆኑ የኮድ02አአ_ሰሌዳ ፈላጊዎች ከነገ ሰኔ 15 ቀን 2014 ጀምሮ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ተገልጋዮች ወይም የኮድ-02 ሰሌዳ ፈላጊዎች በሙሉ መሟላት ያለባቸዉን መረጃዎች በማሟላት በ11ዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመኖርያ አድራሻችሁ ብቻ መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡
ሰሌዳ መስጠት የተጀመረባቸዉ አገልግሎቶችም አዲስ ተሸከርካሪ እና በጨረታ የተገዙ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ የአገልግሎት ለዉጥ እና የፋይል ዝዉዉር አገልግሎት ሰሌዳ መስጠት ሲጀመር እንደሚገልፅም ተነግሯል፡፡

ኮድ 02 አ.አ ሰሌዳ ለመዉሰድ ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች አሟልተዉ በመምጣት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚረዳም ተመላክቷል፡፡

ለበለጠ መረጃ

telegram ገፃችን፡- https://t.me/AddisAbabaDVInfocenter_bot

Facebook ገፃችን፡- https://www.facebook.com/AADVInfoCenter

ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011 666 33 74
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢ-ሜይል፦ aagtpmo@gmail.com

Leave a Reply