“በታቀደ የትራንስፖርት አገልግሎት የተሻሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት”

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አቃቂ ቃሊቲ ትራንስፖርት ቅ/ፅ/ቤት “በታቀደ የትራንስፖርት አገልግሎት የተሻሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል ንቅናቄ ተካሄዷል፡፡
በቀጣይ ሶስት ወራት በትኩረት መሰራት ባለባቸው አምስት ዋና ዋና በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን ንቅናቄ ተደርጓል፡፡
በንቅናቄዉም የተጋረጡ የትራንስፖርት ችግሮችን በመፍታት የተመቻቸ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በእለቱ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይርጋለም ብርሀኔ እንደገለፁት የንቅናቄ መድረኩ ለህብረተሰቡ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በክፍለ ከተማዉ የሚሰጠዉ የትራንስፖርት አገልግሎት ግልፅ ምቹና ተአማኒነት ያለዉ መሆን እንዳለበት በማሳሰብ የንቅናቄ መድረኩ በቀጣይነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
አቶ ይርጋለም አክለዉም ለዚህ የንቅናቄ መድረክ መሳካትና መሳለጥ ጉልህ ሚና ለተጫወቱ ለታክሲ ባለንብረቶች ማህበራት፣ለተራ ማስከበር ማህበራት፣ለትራፊክ ፖሊሶችና ለቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሠራተኞች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቢሮው የአቃቂ ቃሊቲ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ቶማስ ሂርጶ በበኩላቸው የትራንስፖርት ዘርፍ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያሉትን ሁሉንም ዓይነት ተሽከርካሪዎች በመለየት በአግባቡና በስርዓት መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ችግር ያሉባቸውን ተርሚናሎች በመለየት የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና ማስተካከል አለብን ሉት ዋና ስራ አስኪያጁ ለህብረተሰቡ ግልፅና እዉነተኛ መረጃ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የየመስመሩን ታሪፍ በግልፅ በሚታይ ቦታ ለይ ማስቀመጥ፣የተሸከርካሪ የምልልስና የተሳፋሪ የትራንስፖርት ማግኛ የቆይታ ጊዜን ማሻሻል፣ተሸከርካሪዎችን የትራንስፖርት ችግር ባለበት ቦታ በማዘዋወር ማሰራት እና ለተሸከርካሪ ምልልስ እንቅፋት የሆኑትን ቦታዎችና መስመሮች ቀድሞ በመለየት መፍትሔ በመስጠት የተሽከርካሪን የምልልስ ጊዜ በማሻሻል አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ በቀጣይ በትኩረት እደሚሰራ ገልጣል፡፡
ኢንስፔክተሩ አክለዉም በክፍለ ከተማዉ ያሉትን የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች በሙሉ አቅም በመጠቀም በቀን አንበሳና ሸገርን ጨምሮ ከ 72‚000 ህዝብ በላይ ማጓጓዝ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የትራፊክ አደጋና መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ እንደገለፁት ከተማችን በመጠኑም ቢሆን የትራንስፖርት ችግሮች እንዳሉና በተለዩ ምክንያቶች መጠነ ሰፊ የትራፊክ አደጋዎች እንዳጋጠሙ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በዘጠኝ ወራት ዉስጥ 36 የሞት አደጋ፣ 157 ከባድና 80 ቀላል የአካል ጉዳት በድምሩ 1509 አደጋዎች መድረሳቸዉን በማስታወስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትልቅ ሃላፊነት እንዳለብን አዉቀን የመልካም አስተዳደር ንቅናቄውን ማስፈፀምና መፈፀም እንደሚገባ አደራ ሲሉ በአንክሮት አሳስበዋል፡፡
ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 09 11 33 97 24 ወይም 09 10 53 22 73
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢሜይል፦ aagtpmo@gmail.com

Leave a Reply