አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፤ 2014፤ በመዲናዋ ትራንስፖርት ዘርፍ አመራሮችና ሠራተኞች የተሳተፉበት የስነ-ምግባና የሰራተኞች መመሪያ አዋጅ 56/2010 ዙሪያ በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በስልጠናው መዝጊያ ላይ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የጥናትና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወርቁ ደስታ እንደተናገሩት አቅም ማጎልበቻው የምናውቀውን ለማስታወስ ብሎም ወደ ስራ ለመግባት ይረዳል ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ ለተቋም ውጤታማነት እንደሚያግዝ የገለፁት ም/ቢሮ ኃላፊው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከከፍተኛ አመራር እስከቡድን መሪ ያሉ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
እንደዚህ ዓይነት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች በቀጣይነት መሰጠት እንደሚገባቸው የተናገሩት አቶ ወርቁ ሠራተኞች በእውቀትና ክህሎት በማብቃትም ተቋሙን በቴክኖሎጂ እንዲመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም በውስጥ የተቋሙን የመፈፀም ብቃት ለማሳደግ የሚደረገው እንቅስቃሴ አበረታች ነው ያሉ ም/ቢሮ ኃላፊው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬቱ መልካም ጅማሮ መቀጠል አለበት ምስጋናም ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በቢሮው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምባላይ ዘርዓይ በበኩላቸው አቅም ማጎልበቻው ቢሮው እንደአዲስ መልሶ የተደራጀ በመሆኑ አመራሩንና ሠራተኛውን ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስተዋውቅ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በስልጠናውም የስራ ስነ-ምግባር መርሆዎችን፣ የጥቅም ግጭትና የአስቸኳይ ሙስና መከላከል የተመለከቱ ርዕሰ-ጉዳዮች መዳሰሳቸውን አቶ አምባላይ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም በአዋጅ 56/2010 በሠራተኞች መብትና ግዴታ ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻው የተመለከተ ሲሆን ለቢሮው በየደረጃው ላሉ አመራሮች ግንዛቤ በመፍጠር የተቋሙን ግብ ለማሳካት የጋራ እና የተናጠል ሚና እንዲወጡ ያግዛልም ብለዋል፡፡
በስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ እና የቅርንጫፍ ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011 666 33 74
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢ-ሜይል፦ aagtpmo@gmail.com