ቃሊቲ የአውቶቡስ ዴፖ ተመረቀ፡፡

ቃሊቲ የአውቶቡስ ዴፖ ተመረቀ፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8፤ 2012 ዓ.ም፤በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ቃሊቲ የአውቶቡስ ዴፖን በዛሬው ዕለት በይፋ አስመረቀ፡፡

ለዴፖው ግንባታ 789.5 ሚሊዮን ብር በጀት ወጪ ተደርጎበታል፡፡

በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶቡሶችን በተመቻቸ ሁኔታ የማቆም አቅም ያለው ይህ ዴፖ 89 አውቶቡሶችን ከመሬት በታች ማቆም ያስችላል፡፡

ዴፖው በዉስጡ ዘመናዊ ጋራዥን ጨምሮ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎችን ያካተተ ከአንድ ማዕከል ሥምሪት የሚሰጥበት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው፡፡

በተጨማሪም ሁለት የአውቶቡስ ማጠቢያ ማሽንና አራት የነዳጅ መቅጃ ማሽን ያለው ነዳጅ ማደያ እና በአንዴ ለ19 አውቶቡሶች የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ዴፖ መሆን ችሏል፡፡

የአውቶቡሶችን ውጭ አካል ቀለም የመቀባት አገልግሎት መስጠት የሚችል ዘመናዊ የአውቶቡስ ዴፖ ነው፡፡

የአውቶብስ ዴፖውን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በይፋ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ዴፖውን ከመረቁ በኋላ እንደተናገሩት የዛሬው ምረቃ የከተማ አስተዳደሩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የመጨረስ ግብ አንድ አካል መሆኑን አስታውቀዋል።

በከተማዋ አስተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ እና የሚገነቡ ፕሮጀክቶች መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አወቀ ሀይሌ በበኩላቸው ዴፖው አስተዳደሩ በቀጣይ ለሚገዛቸው 3 ሺህ አውቶቡሶች አገልግሎት እንደሚሰጥ በምረቃው ላይ ገልጸዋል።

የአውቶብስ ዴፖውን በቀጣይ ለማስፋፋትም አጠገቡ ሁለት ሄክታር መሬት መከለሉንም ጠቁመዋል።

Leave a Reply