መርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

መርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012፣ መርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ተርሚናሉ 84 በመቶ የደረሰ ሲሆን፥ በ2012 በጀት አመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው፡፡

የአውቶቡስ ተርሚናሉ የተሳፋሪዎችን ምቾት በመጠበቀ በርካታ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል፡፡

ተርሚናሉ በአንዴ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል፤ የራሳቸው መግቢያ እና መውጫ ያላቸው ሁለት ወለሎችን አካቷል፡፡

በዋናነት የአውቶቡስ መጠበቂያ ቦታ፣ የትኬት ሽያጭና የተሳፋሪ መጫኛና የማራገፊያ ቦታ ያሉት ሲሆን፥ ዘመናዊ ስምሪት አገልግሎትን ጨምሮ የአውቶቡስ መርሃ-ግብርና የአስተዳደር ቢሮዎችንም አካቷል፡፡

ተርሚናሉ በ4,125 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሲሆን፥ በአንድ ሰዓት 6,000 ለሚጠጉ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡

በቀን ከ50,000 እስከ 80,000 ገበያተኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን አገልግሎት እንደሚሰጥ ታሳቢ በማድረግ ተርሚናሉ መገንባቱ በአካባቢ የሚኖረውን የትራንስፖርት እጥረት በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተመደበ 200 ሚሊዮን ብር ግንባታው በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

መረጃው፤ በትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ነው

ለበለጠ መረጃ፤ 251 557 32 66

Leave a Reply