የቢሮው ዳራ

የአዲሰ አበባ ከተማን ፈጣን የሕዝብ ዕድገት ተከትሎ እየጨመረ የመጣው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና እንቅስቃሴ፣ የሕዝቦቿን የትራንስፖርት ፍላጎት በከፍተኛ ፍጥነት ጨምሯል፡፡እየጨመረ የመጣውን የዜጎች የዕለት፣ ዕለት የሥራ እንቅስቃሴና ለትራንስፖርቱ ዘርፍ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የትራንስፖርት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ዘለቂና ቀጣይነት ያላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ  እና የተጀመሩት ፕሮጀክቶች የሚገኙበት የግንባታ ደረጃ የተለያየ በመሆኑ፣ ከተማ አስተዳደሩ፣ በተለይም የአዲስ አበባ መንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮ፣ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በማስተሳሰር ለሕብረተሰቡ ዕለታዊ የትራንስፖረት አገልግሎት ፍላጎት  ትርጉም ባለው አኳኋን ምላሽ ለመስጠት በጋራ አቀናጅቶ በመንቀሳቀስ ለይ ይገኛል፡፡

ስለዚህ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀቸቶችን (ተጀምረው በተለያዩ ደረጃ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች፣ በጥናት ደረጃ ላይ የሚገኙ፣ እና ወደፊት በጥናት ተለይተው የሚፈጠሩ ፕሮጀክቶቸን) ለማስተባበርና አስተሳስሮ የሚመራ ተቋም በማስፈለጉ፣ የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ በደንብ ቁጥር 55, 2005 በከተማው አስተዳደር ተቋቁሟል፡፡ጽ/ቤቱ በዘርፉ የላቀ ቴክኒክ፣ ክህሎትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን በማሰባሰብ፣ በከተማዋ የተለያዩ ተቋማት ሥር የተደራጁ የመንገድና የትራንስፖርት ፕሮግራሞችን የመምራት እና የማስተባበር ሚና ተሰጥቶታል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፍ የታዩ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታት እና ዘርፉን በጥናትና ምርምር የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ ረገድ ጽ/ቤቱ ለከተማ አስተዳደሩ እና ለመንገድና የትራንስፖርት ቢሮ  የላቀ ምክር፣ በጥናት ላይ የተመሠረተ አስተያየት የመስጠት፣ እና ስትራቴጂያዊ ዕቅድ የማዘጋጀት ሚና ተሠጥቶታል፡፡ እነዚህ ጥናትና ምርምሮች የትራንስፖርት ዘርፉን የዕለት፣ ዕለት መሠረታዊ ችግሮች በመፍታት እና ከዚህም ጎን ለጎን በዘርፉ ያሉ የባለድርሻ አካላትን አቅም በመገንባት የከተማችንን የትራንስፖርት ሥርዓት ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ የሚሠሩ ናቸው፡፡ስለዚህ  የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና ተግባራዊ በማድረግ፣በትራንስፖርት ዘርፍ ያሉ ወቅታዊ እና የረጂም ጊዜ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚሠራ ተቋም ነው፡፡   

የቢሮው ተቋማዊ መዋቅር