የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዉ ማህበረሰብ ባሉት የትራንስፖርት አማራጮች የመጠቀም ልምድ ማዳበር እንደሚገባዉ ተጠቆመ
ሀምሌ 16/2016 ዓ.ም (ትሎሚ) የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዉ ማህበረሰብ ባሉት የትራንስፖርት አማራጮች የመጠቀም ልምድ ማዳበር እንደሚገባው የስምሪት ባለሙያዎች ጠቁመዋል።
በተለይ በስራ መውጫ ሰዓት ላይ አንዳንድ አካባቢዎች ብዙ ተሽከርካሪዎች ተሰልፈዉ እያሉ የትራንስፖርት ፈላጊዉ ተሰልፎ ትንንሽ ታክሲዎችን ለረጅም ሰዓት እንደሚጠብቁ አስተባባሪዎች መታዘባቸዉን ተናግረዋል።
ለአብነትም መነሻቸዉን ፒያሳ በማድረግ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት ለመስጠት የቆሙት የአንበሳ አውቶቢስ፣ የሸገር ፣ የፕብሊክ ትራንስፖርት፣ አገር አቋራጭ እና መለስተኛ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ተሳፋሪዎችን እንደልብ ባያገኙም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
የትራንስፖርትን እጥረት ለመቅረፍ ሲባል በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስተባባርነት የተጀመረዉ ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት
ድረ ገጽ፡ www.motl.gov.et
ፌስቡክ https://www.facebook.com/EthiopianTransport?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም:ቴሌግራም: https://t.me/ministryoftransportethiopia
Email: transportethiopia@gmail.com