ስኬታችን በአግልግሎት አሰጣጣችን ህብረተሰብን ማርካት ነው
አቶ ደረጄ በየነ የፀሀይ ታክሲ ማህበር ሰብሳቢ
የፀሀይ ታክሲ ማህበር ቦርድ አባላት በቀን 19/12/2014 ለመጀመርያ ጊዜ የማህበሩን የ2015 የስራ እቅድ ከየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ፣ ከትራፊክ ፖሊስ ተወካይ፣ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ተወካይና በዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ተወያይተው አፅድቀዋል፡፡
የፀሀይ ታክሲ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ደረጄ በየነ የማህበሩን የ2015 በጀት አመት የስራ እቅድና የ2014 የስራ አፈፃፀም ለተወያዮቹ አቅርበዋል።
ማህበሩ በ21 መስመሮች በአመት አራት ጊዜ ለተሸከርካሪዎች የሽክርክሪት መስመር በመስጠት አባላቱ በተሰጣቸው የጉዞ መስመር እና ቢሮው ባወጣው ህጋዊ ታሪፍ መሰረት እንዲሰሩ እንዲሁም በሀገራዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎች ጭምር ግንባር ቀደም በመሆን የዜግነት ግዴታዎች በመወጣት ማህበሩ ጥሩና አበረታች የስራ እንቅስቃሴ በ2014 በጀት አመት እንደነበረው በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የማህበሩ የቦርድ አባላትም በቀጣይ በ2015 በጀት አመት ከአቻ ማህበራትና ከትራንስፖርት ዘርፉ ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ለአባላቱ ግንዛቤ ማስጨበጫዋችዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ስራዎችን ለማከናወን በእቅድ መያዙን የማህበሩ ሰብሳቢ ገልፀዋል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና የተሻለ ለማድረግ በማህበሩ ያሉ አገልግሎት ሰጪዎች የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሰው በስነምግባር የታነፁ ሆነው እንዲሰሩ በስልጠናም ጭምር መታገዝ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።
በመጨረሻም ለፀሀይ ታክሲ ማህበር ስኬትና ሙያዊ ድጋፍ ለነበራቸው ለየካ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ጀማልና ለማህበሩ ቦርድ አባላትን ጨምሮ ማህበሩ የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።