የጭነት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ከ7 ቶን በታች የመጫን አቅም ያላቸው የተሽከርካሪ ባለንብረቶች እና ማህበራት ቢሮው እየሰጠ ያለው አገልግሎት ቀልጣፋ እና ለተገልጋዩ ምቹ መሆኑን ተገልጋዮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የትንቢት ደረቅ ጭነት ባለንብረቶች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሳያስ ንጉሴ ቢሮው ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠቱ የተገልጋዩን እንግልት የቀነሰ ነው ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ አገልግሎቱን እየተገለገሉ ያገኘናቸው ከትራኮን ትሬዲንግ የመጡት አቶ አህመድ ሰይድ አገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ ከመሆኑ ባሻገር በሰፊ ቢሮ ለተጠቃሚው ማረፊያ ተዘጋጅቶ፣ አገልግሎቱ በአንድ ማዕከል መሰጠት መቻሉ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።
በመጨረሻም የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ወደ ህጋዊ ስርዓት ለማስገባት በትኩረት እየሰራ ሲሆን፤ እስከ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ ሁሉም ባለንብረቶች እና ማህበራት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማውጣት እንዳለባቸውም ቢሮው ያሳስባል፡፡