በህጋዊ የመንገድ ተጠቃሚነት ለመንገድ መሠረተ ልማቶች ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ የእያንዳዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ከአምስቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውስጥ
• ከአራት ኪሎ እስከ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን መታጠፊያ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት እንዲሁም
• ከቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም በደጎል አደባባይ እስከ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን አቅጣጫ መንገዱ በትናንትናው ዕለት ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በህጋዊ የመንገድ ተጠቃሚነት ራስንና ሌሎችን ከመንገድ ትራፊክ አደጋ ስጋት በመጠበቅና ለመንገድ መሰረተ ልማቶች ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ የእያንዳዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቦ ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሔድ ክልክል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡