የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና በቴክኖሎጂ ለማዘመን በአዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀት በድጋሚ ሊዋቀር ነው።

የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እና የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ እያደረገ ባለው ሪፎርም ወይም መዋቅራዊ አደረጃጀት መነሻነት የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አሁን በድርጅቱ አሁን እየተስተዋለ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈታ ስለመሆኑ ዛሬ ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ ተገልጿል።

ሪፎርሙም ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ ለማሳካትና አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እንዲሁም የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃለፊዎች አቶ ዳኛቸው ሽፈራውና አቶ አካሉ አሰፋ እንዲሁም የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው አለሙ ውይይቱን በጋራ መርተዋል ።

በመጨረሻም ድርጅቱ የሰራተኛ ድልድልና መዋቅራዊ አደራጃጀት የሚያስተባብሩ የሰራተኛ ተወካይ ኮሚቴዎች ተመርጠዋል፡፡

በውይይቱም የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዴፖ ስራ አስኪያጆችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

#transportbureau

Leave a Reply