የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የማንዋል የትኬት ሽያጭ ስራን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በዘመናዊ የትኬት መቁረጫ ማሽን (Hand helding Ticketing Terminal) በሙከራ ትግበራ በሸጎሌ ዴፖ በሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙ 235 የከተማ አውቶብሶች ላይ ተግባራዊ አድርጓል።
የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የኢንተለጀንት ትራንስፖርት ሲስተም ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስባቸው መንግስቴ ድርጅቱ ከተማዋን የሚመጥን ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋትና በድርጅቱ የሚስተዋሉ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመቀነስ የአውቶብስ ትኬት መቁረጫ ማሽኑ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
የትኬት ማሽኑም ለተሳፋሪው የጉዞ ርቀትን መነሻ ያደረገ ታሪፍ ክፍያ፣ ለትኬት ህትመት ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ይቀንሳል፣ የተገልጋዩን ሰዓት በእጅጉ ይቀንሳል።
በተጨማሪም ማሽኑ ከእጅ ንክኪ የጸዳ አሰራርን በመፍጠሩ የተሽከርካሪውን የጉዞ እንቅስቃሴን ለመከታተል ያስችላል፣ የተሳፋሪውን ቁጥርና የእለት ገቢን ያሳያል እንዲሁም አገልግሎት የተሰጠበትን ሰዓት ጭምር ሲስተም ላይ የሚያሳይ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አስረድተዋል።
በሙከራ ትግበራው በተገኘው ተሞክሮ መነሻነት ሙሉ በሙሉ በቀሪ አውቶቡሶች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።
ለተጨማሪ መረጃ
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!