(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ 30/2016 ዓ.ም)
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በትላንትው እለት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በመገኘት የቢሮውን የ ዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም በመገምገም የሱፐርቪዥን (የድጋፍና ክትትል) አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክንፈ አዲስ ቢሮውና ተጠሪ ተቋማቱ በዘጠኝ ወር ዘርፉን ለማሻሻል የተሰሩ አበረታች ስራዎች መኖራቸውን ገልፀው፤ ከህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶችን ማሻሻል፣ የቁጥጥር ስርዓቱን ማጠናከር፣ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ይገባዋል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ህብረተሰቡ የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኝ ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ቋሚ ኮሚቴው ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ እያደረገ ያለው ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ ይገባል ብለዋል።
በውይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት፣ የክፍለ ከተማ ዘርፉ ኮሚቴ አመራሮች፣ የህዝብ ክንፋ አመራሮችና የትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የመስክ ሱፐርቪዥኖችም በቀጣይ ቀናት የሚቀጥሉ ይሆናል።