አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ዘርፉ 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሃ-ግብሩም 2 ሺህ የሚሆኑ የቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች፣ የ11ዱም የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ የታክሲ ባለንብረቶች ማህበራት፣ የሃይገር ባለንብረቶች ማህበራት፣ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ማህበራት፣ የአደይ አበባ እና የሞተር ሳይክል ማህበራት በችግኝ መትከያ ቦታ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ አዲሱ ማረሚያ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ወቅት ንግር ያደረጉት የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት የሺጥላ እንደተናገሩት ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንዲፀድቁ ተገቢው እንክብካቤ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም እንደትራንስፖርት ዘርፍ እንዲህ ዓይነት በጎ ተግባራት መፈፀም ተገቢ ነው ያሉት ቢሮ ኃላፊው በቀጣይም በሁለንተናዊ የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፎችና ስራዎች አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል፡፡
ለአገር ያለንን ቁርጠኝነት የምናረጋግጥበት አንዱ ማሳያ እንዲህ ዓይነት ዘመቻዎችን መሳተፍ ነው፤ ይህንን ደግሞ በየትኛውም መስክ በላቀ ማስቀጠል አለብን ሲሉም አቶ ዳዊት አስረድተዋል፡፡
አክለውም በዚህ ረገድ ለአገር የሚጠበቅብንን በማድረግ ተስፋ ያላት ለሁሉም የምትበቃ ኢትዮጵያን ለመገንባት የበኩላችንን ሚና እየተወጣን ነውም ብለዋል፡፡
በእለቱም ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ተሳትፎ ያደረጉ አካላትም የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ ተገቢውን እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በነበሩ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ዓመታት የተተከሉ ችግኞች በአመዛኙ መጽደቃቸው ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ለዚህ ስራችን በቀጣይም የእንክብካቤ ስራ እንድንሰራ ትኩረት እንደሚሻ ማሳያ ነው፡፡
ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011 666 33 74
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢ-ሜይል፦ aagtpmo@gmail.comዘገባው፡-