(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የከቲት 20/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት የቢሮውን ለሙስና ተጋላጭነት ስጋት የሆኑ አሰራሮች እንዲስተካከሉ በማድረግ በሙስና መከላከል ስራው ላይ ለውጥ ለማምጣት በተዘጋጀው የማስፈፀምያ ዕቅድ ዙሪያ የቢሮው የጀነራል ካውንስል አበላት ጋር ዛሬ የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም በተዘጋጀው የማስፈፀምያ እቅድ መሰረት በሙስና መከላከል ስራው ላይ አጠቃላይ የተቋሙ አመራርና ባለሙያዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ፣
ተቋማት ውስጥ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ሊያጋልጡ የሚችሉ አሰራር ስርዓቶችን በማጥናት ወይም እንዲጠኑ በማድረግ የመፍትሔ ወይም ማሻሻያ ሃሳቦችን ማቅረብ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ጥናቱ ባመላከታቸው ግኝቶችና የመፍትሔ ሃሳቦች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩና ኮሚሽኑም ክትትል በማድረግ ያሉ መሻሻሎችን ለመገምገም ያስችለው ዘንድ የተጋላጭነት ቅነሳ እቅድ (Mitigation Plan) መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureau
ድረገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!