(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የካቲት 22/2016ዓ.ም ) ቢሮው ከድሬደዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ባለስልጣን ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችን ለማከናወን እንዲያስችል ልምድ ለመቅሰም ለመጡ የልዑካን አባላት በትራንስፖርት ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎች በተለይም ከአደረጃጀት፣ ከቴክኖሎጂ ትግበራ፣ ከመሰረተ ልማት፣ ከአሰራር ስርዓትና ከህግ ማዕቀፎች አኳያ ልምዱን አካፍሏል፡፡
ከከትራፊክ እንቅስቃሴዎች ጋር ተያይዞ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ፣ ከመኪና ማቆሚያ አሰራር፣ ከትራፊክ ፍስት አንፃር፣ ከመንገድ ላይ ምልክቶች አጠቃቀም አንፃር እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ማሳየት የተቻለ ሲሆን፤ በአሽከርካሪ ተሸከርካሪ ዘርፍም የመንጃ ፍቃድ አወጣጥ እና የተሸከርካሪ አገልግሎትን በራስ ዓቅም በበለፀጉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች በዘመናዊ መልክ እየተከናወኑ ያሉትን ስራዎች ተመልክተዋል፡፡
በቢሮው እየተከናወኑ ያሉት በቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶች፣ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎች እና ለብዙሀን ትራንስፖርት እየተሰጠ ያለው ትኩረት አበረታች መሆኑን የገለፁት የልዑካን ቡድኑ በቀጣይ የድሬደዋ አስተዳደር የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ባለስልጣን ለሚያከናውናቸው የትራንስፖርት ለውጦች ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረውም አስታውቀዋል፡፡
አባላቱ በገለፃ፣ በውይይት፣ በመስክ ዕይታ፣ በሰነዶች እና በጉብኝት ተሞክሮዎችን እንዲቀስሙም ተደርጓል፡፡
ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!