የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ያብባል አዲስ የሰው ተኮር ስራዎቻችን የለውጡ ውጤታማነት ማሳያዎች መሆናቸውን በመግለፅ፤ ለአቅመ ደካሞች እና አረጋዊያን እንዲደርስ የተቀረፀው ፕሮግራም የብዙዎችን ህይወት በዘላቂነት በማሻሻል የከተማዋን መልካም ገፅታ የሚገነባ ነው ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ቤቶችን ከ2.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የሚታደሱ መሆኑን ገልፀው፤
በአጭር ጊዜ በጥራት በመስራት ለነዋሪው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ስራ አስፈፃሚ አቶ ደህንነት ገብሩ በወረዳው ዛሬ የሚታደሱት ቤቶች የበጎነት ተምሳሌት መሆናቸውን በመግለፅ፤ ቢሮውና የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ባለፈው በጀት አመትም ወረዳው ላይ 6 የአቅመ ደካማ ቤቶችን አድሰው ለነዋሪዎች ማስረከብ መቻላቸውን አስታውሰዋል።
በመርሀ-ግብሩም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ፣ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አካሉ አሰፋ፣ የክፍለ ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎና የወረዳው አመራሮች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የቢሮና የከተማ አውቶብስ አመራሮችና የወረዳው ነዋሪዎች ተሳትፈል።
ለተጨማሪ መረጃ
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!