(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም) በአደዋ የተፈፀመ ታሪክን፣ጀግንነትን ፣ፅናትን መታሰቢያ ታስቦ የተሰራው የአደዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ባሻገር ህብረተሰቡ ደህንነቱ ተጠብቆ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኝበትን የከተማ አውቶብስ ከትላንት ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
አገልግሎቱን ያስጀመሩት የትራንስፖርት ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አቶ አርጋው በቀለ የከተማ አስተዳደሩ ለትራንስፖርቱ መስኩ በሰጠው ልዩ ትኩረት መነሻነት ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመሆን ቀድሞ በፒያሳ እና አከባቢው ሲሰጡ የነበሩ አስር የከተማ አውቶብስ መስመሮችን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም በአንድ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ብለዋል።
ህብረተሰቡም በሙዚየሙ ምስራቅ ጀግኖች በር በመግባት ወደ አየር ጤና፣ ካራ ቆሬ፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ ሳሪስ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ አጃምባ፣ ጀሞ 3፣ ሃና ማርያም፣ ቱሉዲምቱ እና ዩኒሳ የሚሄዱ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉም ተጠቁሟል።
ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://
ዌብ ሳይት:-www.aactb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!