የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመሳተፍ አሻራቸውን አኑረዋል::
በዛሬው የአንድ ጀምበር መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ጨምሮ የቢሮና የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት አመራሮችና ሰራተኞች፣ የኮልፌ ወረዳ 6 አመራሮች፣ የሞተር ሳይክል ባለንብረቶችና የአዲስ አበባ ታክሲ ማህበራት የአንድ ጀንበር አሻራቸውን በኮልፌ መንዲዳ ህዳሴ ፖርክ ላይ አኑረዋል።