(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 07/2015 ዓ.ም)
የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቀደም ሲል በማንዋል ሲሰጥ የነበረውን የተሽከርካሪ የቦሎ አገልግሎት ከሰኔ 5/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሲስተም አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳወቀ።
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሽከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ተመርምረውም ብቃት ሳይኖራቸው ብቃት እንዳላቸው ተደርጎ የብቃት ማረጋገጫ ቦሎ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎች በመኖራቸውና አሰራሩን በቴክኖሎጂ ማዘመን በማስፈለጉ አገልግሎቱን በሲስተም አድርገነዋል ብለዋል።
አገልግሎቱም ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ እውቅና በሰጠናቸው የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት የሚሰጥ ሲሆን፤ የምርመራውም ውጤት ከሰው ንክኪ በፀዳ መልኩ በሲስተም በቀጥታ ለባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እንደሚላክ ኃላፊው ገልፀዋል።
በተጨማሪም የተመረመረውን የተሽከርካሪ ሰሌዳ ቁጥር ባለሙያዎች ሲያስገቡ የመረመረው የምርመራ ተቋም ስምና ውጤት በትክክል በሲስተም ተረጋግጦ የቦሎ አገልግሎት እንሚሰጥ ተገልጿል፡፡
በከተማዋ የሚገኙ የተሽከርካሪዎች የምርመራ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸውን ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ እንደሚያከናውኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳውቋል።