(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ12/2016ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማትን እቅድ አፈፃፀም ክትትልና ድጋፍ መነሻነት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሄዎችን መሰረት አድርጎ በክትትልና ድጋፍ የታዩ ችግሮችንና የተገኘ ውጤትን የጋራ አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክንፈ በትራንስፖርት ቢሮና ተጠሪ ተቋማቱ የተገኙ ውጤቶችን በሰነድ አቅርበዋል።
በሰነዱም ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ፣ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖርና የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትን ብቃት ተገቢ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በምልከታው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መስመር መቆራረጥ፣ የስምሪትና ቁጥጥር ስርዓት፣ ከታሪፍ በላይ ማስከፈል፣ የአገልጋይነት መንፈስ አነስተኛ መሆንና ሌሎች በዘርፉ የሚስተዋሉ አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች መኖራቸውን ከግኝቱ ለአብነት የተጠቀሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው፡፡
በመጨረሻም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ቢሮው በሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ቢሮው እንደሚሰራ ገልፀዋል።