አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 26፤ 2015 ዓ.ም፤ በበጀት ዓመቱ በ9 ወራት ውስጥ በትራንስፖርት የአገልግሎት አሰጣጥና በዘርፉ በሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በትኩረት በመስራት አመርቂ ለውጥ ማምጣት መቻሉን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የለሚኩራ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ ረዳት ኢንስፔክተር ቶማስ ሄርጶ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ቅርንጫፍ ፅፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ማህበራትና ከቢሮው ጋር በመቀናጀት በርካታ አመርቂ ስራዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መሰራት መቻሉን፣ ህግ ተላልፈው በተገኙ 2,359 አጥፊ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና በቀጣይም አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ለማድረግ እንደሚስራ ገልፀዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በሙያዊ ስነ-ምግባርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ እንዲፈጠር ቢደረግ በተጠማሪም ከአጎራባች ክፍለ ከተሞች ጋር በመናበብና ስራዎችን የጋራ በማድረግ መስራት እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱም የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ከትራፊክ ፖሊስ፣ ከኮሚኒቲንግ ፖሊስ፣ የክፍለ ከተማው ትራፊክ መኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ከደንብ ማስከበር፣ ከታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራት፣ ከታክሲ ተራ አስከባሪ ማህበራት፣ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በድምሩ 125 የሚደርሱ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ ለሚኖራችሁ አስተያየትና ጥቆማ
በነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ይጠቀሙ!!