የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በግል ትምህርት ተቋማት የተማሪ አውቶብስ አገልግሎት እንዲያመቻቹ ከትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣንና የግል ትምህርት ቤት ባለንብረቶች ጋር ውይይት አደረጉ።
በውይይቱም ለተማሪዎች በተለየ መልኩ የሰርቪስ አገልግሎት ማዘጋጀት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑና በትምህርት ገበታቸው በሰዓታቸው እንዲደርሱ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደደሚኖረው ተገልጿል።
በተጨማሪም ትምህርት ቤቶች አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችለውን አሰራር ለመዘርጋት በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችን ይዞ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚመክሩ የስራ ኃላፊዎች አንስተዋል።
በውይይቱም የቢሮው ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች፣ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የግል ትምህርት ቤት ባለንብረቶች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!