የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ማዕቀፍ ሊኖራቸው ይገባል ተባለ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት እንዳስታወቀው የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ማዕቀፍ ሊኖራቸው ይገባል ሲል አስታውቋል።

በክፍለ ከተማው በባጃጅ ስርዓትና ህጋዊነት ማዕቀፍ ዙሪያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ባለ ሶስትና ባለ አራት እግር የባጃጅ ተሽከርካሪዎች የፀጥታ ስጋትና የወንጀል ምንጭ በመሆን በህብረተሰቡ ላይ ስጋት ፈጥረዋል ተብሏል።

ህጋዊ ማቀፍን መሰረት አድርገው የሚሰሩ ማህበራት ቢኖሩም በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ወንጄል እየተፈፀመባቸው መሆኑን በመረጃና ማስረጃ መረጋገጡን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም ህጋዊ አሰራርና አደረጃጀት እስከሚፈጠርላች ህገወጥ የሆኑ ባጃጆች ብቻ ከስምሪት ውጭ ሆነው ይቆያሉ ብለዋል።

የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተቀናጀ፣ በተነበበና መመሪያን ማዕከል ባድረገ አሰራር ወደ ተግባር እንገባለን ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የስራ አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።

በውይይቱ ላይ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር አመራሮች፣የፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎችና የትራንስፖርት ቢሮ ተወካዮች ተገኝተዋል።

#laftocommunication

Leave a Reply