አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18፤ 2014፤ በመዲናዋ የሚገኙ የሞተር ሳይክል ማህበራት ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር በተገቢው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው አሰራር እና መመሪያዎችን በመፈተሽ የማሻሻል ስራውን እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ማህበራቱ የሚጠበቅባቸውን ግዴታዎች መወጣት እንዳለባቸውም ቢሮው አንስቷል፡፡
ቢሮው ከፀጥታ መዋቅሩ እና ከሞተር ሳይክል ማህበራት ጋር የጋራ ፎረም በመመስረት በከተማዋ ሰላምና ደህንነት በጋራ ለመስራት ጭምር በውይይቱ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ለዚህም የተጠናከረ የማህበራት አደረጃጀት መፍጠር እና በወንጀል የሚሳተፉትን ለይቶ እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል የሞተር ሳይክል ማህበራቱ ሚና የጎላ ነውም ተብሏል፡፡
ዝርዝር መረጃዎቹን ከታች ይመልከቱ…
ዘገባው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 011 666 33 74
የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/tpmo
ኢ-ሜይል፦ aagtpmo@gmail.com