(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 08/2015 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻል ከተቋቋመው ግብረ-ሃይል ጋር በጋራ በመሆን በ15 ቀናት የተሰሩ ስራዎችን ዛሬ ገመገመ።
በግምገማውም በክፍለ ከተማው በትራንስፖርት አገልግሎቱ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቅንጅትና በጥምረት በተቋቋመው ግብረ ሀይል በመሠራቱ ለውጦች መመዝገባቸው ተገልፆል።
የለሚኩራ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ረዳት ኢንስፔክተር ቶማስ ሄርጶ በክፍለ ከተማው የመልካም አስተዳደር ችግር የሆኑትን በጥናት በመለየትና ግብረኃይል በማቋቋም ወደ ኦፕሬሽን ስራ መገባቱን ገልፀዋል።
በዋናነትም ከትራንስፖርት ቢሮ ፈቃድና እውቅና ውጪ አገልግሎት በሚሰጡ ህገወጥ የባጃጅ አሽከርካሪዎች፣ ከተቀመጠው ህጋዊ ታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉና ለትራንስፖርት አገልግሎቱን በሚያስተጓግሉ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።
ኢንስፔክተር ቶማስ ሂርጶ የተቋቋመው ግብረ ሀይል የቁጥጥርና የክትትል ስራውን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚያቀጥልና በየ15 ቀናት የመጡ ለውጦች እንደሚገመገሙ ተናግረዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ሲሳይ ሰኔ በግብረ ሀይሉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የተሰራውን ስራና የመጣውን ለውጥ አድንቀው ቅንጅታዊ አሰራሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በአንክሮ ገልፀዋል።
በመጨረሻም የክፍለ ከተማው ፖሊስ አባላቶች፣ የለሚኩራ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት፣ ደንብ ማስከበር፤ ሠላምና ፀጥታ፣ ትራፊክ ፖሊስ፣ የሁሉም ወረዳ አመራሮች እንዲሁም የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሠራተኞች በ15 ቀን የኦፕሬሽን ስራው ላይ ተሳትፈዋል፡፡