(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ መጋቢት 06/2016ዓ.ም) ሁለተኛው ዙር የባህሪና የክህሎት ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ወቅት የቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ እንደተናገሩት ስልጠናው ሰራተኞች የባህሪና ክህሎት ክፍተቶቻቸውን የሚሞሉበትና በተመደቡበት የስራ መስክ ላይ ውጤታማ የህዝብ አገልጋይ እንዲሆን የሚያስችል ነው፡፡
ቢሮው በቀጣይነት የትራንስፖርት አቅርቦት ችግሮችን የመፍታት እና የማሳደግ ስራ፣ የቁጥጥር ስርዓቱን የማጠናከር፣ የግል ባለሀብቶችን ተሳትፎ የማሳደግ፣ የመሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ እና በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ የህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን የማስፋፋት ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራባቸውም አቶ ምትኩ አስታውቀዋል፡፡
ሰልጣኞችም ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው የህዝብ አገልጋይነታቸውን በማጠናከር አስተዳደሩ ለተያያዘው የሪፎርም ትግበራ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡
ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://
ዌብ ሳይት:-www.aactb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!