በግምገማችን ለስራ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት የጀመርናቸው ስራዎቻችን ያሉበትን ደረጃ የለየን ሲሆን ውጤት ካገኘንባቸውና ካሳካናቸው ስራዎቻችን ውስጥ የአመራር የሃሳብ እና የተግባር አንድነት በመገንባት አመራሩ ስራ ላይ እንዲያተኩር መደረጉ ፣የከተማችንን ገጽታ ያሻሻሉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርጉ ትልልቅ እና ታሪካዊ ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ፣ በርካታ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኰኖማዊ ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ የሰው ተኮር ስራዎቻችን የከተማችንን ነዋሪዎች ችግር ያቃለለ መሆኑን ማረጋገጠሰ ፣ የከተማችንን ልበ ቀና ባለሀብቶችን በማሳተፍ የሰራናቸው የበጎ ፍቃድ ስራዎቻችን ዝቅ ብለን ከመረጠን ህዝብ ጋር እየመከርን እያዳመጥን ምላሽ የሰጠናቸው የህዝብ ጥያቄዎች እንዲሁም የገቢ አሰባሰባችን አበረታች ሲሆኑ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተግባብተናል።
አመራራችን ተቀናጅቶ ያሳካቸው ስራዎች መልካም ቢሆንም በቀሪ ወራት ከህዝብ ችግር እና ጥያቄ አንፃር ለመረጠን ህዝብ የምንሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል በሰው ሃይል እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በልህቀት መከወን፣ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ሁሉ ማጠናቀቅና የከተማዋን አጠቃላይ መሠረተ ልማት ማሻሻል፣ የኑሮ ውድነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ስራዎች ላይ መስራት፣ ለወጣቶቻችን ሰፊ የስራ እድል መፍጠር እንዲሁም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማስወገድ ረገድ በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን መስራት እንዳለብን ተስማምተናል::
የአመራራችንን አቅም እየገነባን ተቋማት በአሰራርና በአደረጃጀት በማጠናከር ለኑሮ እና እንደ ስሟ አበባ የሆነች ከተማ መገንባታችንን አጠናክረን እንቅጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ