———-
በዚህ 6ወር 200 ሄ/ር መሬት ለማዘጋጀት ታቅዶ 361.84 ሄ/ር ተከናውኗል፤ ባለፈው ዓመት በከተማ ደረጃ በተካሄደው የመሬት ኦዲት የተለዩ 11ሺህ 844 የመንግስት ቦታ/ ፕሎቶች/ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርገዋል፤
በ6 ወሩ 135 ሄ/ር የለማ መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ 149.11 ሄ/ር ለማስተላለፍ ተችሏል፤
ለመልሶ ማልማት 2,028,123,370 ብር፤ ለ 825 የልማት ተነሺዎች ምትክ ቤትና ቦታ ለመስጠት ታቅዶ 1,228 ተሰጥቷል፣ 1203 ቤቶች ምትክ ቤት ተሰቷል፣ የካቢኔ ውሳኔ ያገኙ ለ194 ባለ ይዞታዎችን ጨምሮ 8,788 ባለይዞታዎች መብት ለመፍጠር ታቅዶ ለ13,689 መብት መፍጠር ተጭሏል፤
ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተቀናጀ የመሬት መረጃ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በታቀደው መሰረት የከተማውን ሙሉ ይዞታ ማህደር 726 ሺህ 150 ማህደራት ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ሆኖ ወደ ሰርቨር አፕ ሎድ ተደርጓል፤
ክፍለ ከተማ በተበታተነ ሁኔታ የተደራጀ የመሬት መረጃ / ቤዝ ማፕ መረጃ/ በአንድ የመረጃ ቋት በጂአይኤስ እንዲተዳደር የማድረግ ሥራ ተሰርቷል፤
የይዞታ አገልግሎት በቴክኖሎጂ ለመስጠት የሚያስችል የITMIS ሲስተም ለምቶ ለትግባራ ዝግጁ ተደርገዋል፤
ለመልካም አስተዳደር ችግሮች እና ብልሹ አስራር ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ 14 የመሬት ደንቦች እና መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ማሻሻል የሚያስችል ስራ ታሰርቷል፤
መሬት በምደባ ከማስተላለፍ አንፃር ለተለያየ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶችና ተቋሞች የሚውል 55ሄ/ር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ 73.11ሄ/ር (133%) መሬት ማስተላለፍ ተችሏል፤
የአካባቢ ልማት ፕላኖችን ከማዘጋጀት አንፃር ቀደም ሲል ተጠናቀው በከተማ አስተዳደሩ እንዲፀድቁ የቀረቡ 1,365 ሄ/ር የሚሸፍኑ 13 ቦታዎች ፀድቀው ለትግበራ ተሰራጭተዋል፤
በ6ወሩ የታቀዱ 231.72 ሄ.ር. የሚሸፍኑ 5 የአካባቢ ልማት ፕላኖች 100% ተጠናቀው ለውሳኔ ቀርበዋል፡፡ እንዲሁም የከተማችንን ልማቶች ሊያስተሳስሩ የሚችሉ 1,033 ሄ.ር. የሚሸፍኑ የኮሪደር ልማት ተጠናቆ ይገኛል፤
የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከማዘጋጀት አንፃር ለ2 ሺህ 492 አርሶ አደርና የአርሶ አደር ልጆች ለመኖሪያ እና ለእርሻ አገልግሎት መብት ለመፍጠር ታቅዶ ለ2,306 (92.46%) የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማዘጋጀት ተችሏል፤
በከተማ ግብርና ስራዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ የነበረውን 511,006 ነዋሪ በእንስሳትና በእፅዋት ሃብት ልማት ለማስቀጠል ታቅዶ 455,940 (89%) ማስቀጠል ተችሏል፣
አዲስ 102,491 የቤተሰብ ፍጆታ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 80,941 /79%/ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፣