የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ9ኛው የከተሞች ፎረም ልዩ ተሸላሚ ሆነ!!
1መቶ 24 ከተሞች የተሳተፉበት የከተሞች ፎረም ከየካቲት 9 -14 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ሲካሄድ እንደ ነበር ይታወሳል።
ፎረሙ በዛሬው እለት ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ልዩ ተሸላሚ በማደረግ ሲሆን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ለከተማ አስተዳደሩ አበርክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተሞች ፎረም ላይ የነበረው ተሳትፎ እጅግ ውጤት ተኮርና ለሌሎች ከተሞች ተሞክሮን ያቋደሰ ስለ መሆኑ አቶ መኮንን ያኢ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ም/ቢ/ኃላፊ ገልፀዋል። በተጨማሪም የከተሞች እርስ በእርስ ግኑኝነቶችን ያጠናከረና ልምድ የመለዋወጥ እድል ያመቻቸ ፎረም እንደነበረም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን የብልፅግና ተምሳሌት ከተማን የመፍጠር ራዕይን አንግባ በርካታ አመርቂ ስኬቶችን እያስመዘገበች የምትገኝ ከተማ መሆኗን የገለፁት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ ሲሆኑ፣ በፎረሙ ላይ በተለያዩ መንገድ የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ ለጎብኚዎችና ለተሳታፊ ከተሞች በማስተዋወቅ ማካፈላቸውን ገልፀዋል።
ለተጨማሪ መረጃ
Linkedin https://www.linkedin.com/…/addis-ababa-communication…/
Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100066583024934
Youtube https://www.youtube.com/@addisababacommunication9471
Tik Tok https://www.tiktok.com/@aacommu
Telegram https://t.me/AAcommu
Website https://www.cityaddisababa.gov.et
Reddit https://www.reddit.com/r/humanita/s/04A4PQ63Ou Twitter https://twitter.com/AddisAbabaCity1