አዲስ አበባ፤ መጋቢት 04፤ 2015 ዓ.ም፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በቅርቡ ወደ ተቋሙ የተቀላቀሉ 70 አዳዲስ የትራንስፖርት ቁጥጥርና የፋይናንስ ሠራተኞችን ወደ ስራ የሚያስገባ የቲወሪ እና የተግባር ስልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡
አቅም ማጎልበቻው ሠራተኞቹን በስነ-ምግባር የታነፁ፣ በአግባብ ጊዜያቸውን የሚጠቀሙ እና የመንግስት ሰራተኞችን መመሪያ ቁጥር 56/2010ን በተገቢው በማወቅ መብትና ግዴታቸውን በተግባር የሚያውሉ እንዲሆኑ ስልጠናው የጎላ ሚና ይኖረዋል፡፡
በተለይ አቅም ማጎልበቻው ወደ ስራ ዓለም በሚገቡበት ወቅት በስራ ላይ ሊያጋጥማቸው የሚችሉትን ሁኔታዎች በተግባር ጭምር በመስክ ላይ አቅም የሚፈጠርላቸው መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ስልጠናው ከዛሬ ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ለ3 ቀናት የቲወሪ፣ ለ2 ቀናት ደግሞ የተግባር በመስክ ላይ ስልጠናው እንደሚሰጥ ተገልፆል፡፡
በስልጠናውም አዳዲስ 60 የቁጥጥር ሰራተኞች፣ 10 የፋይናንስ ሰራተኞች በድምሩ 70 ወደ ተቋሙ በቅርቡ የገቡ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡
መረጃው፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
ለተጨማሪ ጥቆማና አስተያየት፡- በ011-666-33-73 ወይም ነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ይጠቀሙ!!