(ግንቦት 27/2015 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ)
አዲስ አበባ ከተማ የብሉምበርግ ብስክሌት መሰረተ ልማት Bloomberg Initiative for Cycling Infrastructure (BICI) ኢንቨቲቭ አሸናፊ ከሆኑ አስር የዓለማችን ከተሞች ውስጥ አንዷ ሆናለች።
ከ5 አህጉራት 275 ከተሞች ፕሮፖዛል አቅርበው ተወዳድረው ነው 10 ከተሞች የውድድሩ አሽናፊ የሆኑት።
የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ አሸናፊዎቹ ሃገራት ፤ ኢትዮጲያን ጨምሮ ብራዚል ፥ ህንድ ፥ ጣሊያን ፥ አልባኒያ ፥ ኒውዝላንድ ፥ ፖርቹጋል ፥ ኮሎምቢያ ፥ ኬንያ ፥ ሞዛምቢክ ናቸው።
አዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ ትልቁን የሳይክል ጎዳና ለመገንባት የጀመርቻቸው ስራዎችና ወደፊት ይህን ስኬት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ያቀረበችው ፕሮፖዛል አሸናፊ አድርጓታል።
የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልንና ለህዝቡ ተጨማሪ የትራንስፖርት አመራጭ ማቅረብን ታሳቢ ባደረገው በዚህ ኢንሺዬቲቭ አዲስ አበባ ከተማ የ400 ሺህ ዶላር ታገኛለች።
አሸናፊዎቹ ከተሞች ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል::
ከተሞቹ ከብሉምበርግ ኢኒሸቲቭ በሚያገኙት ድጋፍ የብስክሌት መጓጓዣ ጎዳናዎች በመገንባት ለነዋሪዎች ጤና እና ደህንነት ለማጠናከር እንዲሁም ለዘላቂ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያውሉት ነው።