ዛሬ የስምምነት ፊርማ የተከናወነላቸው የከተማችን አዲስ አበባ ዘመናዊና አዲስ ዘመን ፈንጣቂ መንገዶች እውነታዎች !!
• በአጠቃላይ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መንገድ ነው፡፡
• ከ15 – 30 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸውን 3 የመንገድና የድልድይ ግንባታ ያካተተ ነው፡፡
• ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን Intelligent Transport System (ITS) ያካተተ ዲዛይን የተሰራለት ነው፡፡
• የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን በመከናወን ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡
• ከ2.4 – 4 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አለው፡፡
• 2 ሜትር ስፋት ያለው የብስክሌት ብቻ መሄጃ መንገድ አለው፡፡
• 9 የሳይክል ማቆሚያና 3 የሳይክል መከራያ ቦታዎች አሉት፡፡
• ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ የብልህ የትራንስፖርት ስርዓት አለው።
•10 የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ ሲሲቲቪ ካሜራዎች አሉት።
• 2 ቦታዎች ላይ ዲጂታል የትራፊክ መቁጠሪያዎች አሉት።
• ቅፅበታዊ የአውቶቡስ መረጃ ማግኛ ስርዓቶች አሉት።
• ኦፕቲክ ፋይበርና ዲጂታል ዋይፋይ ባክአፕ አለው።
• መዝናኛ ቦታ ተካቷል።
የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ማሻሻያ
• የፈጣን አውቶብስ መስመር (BRT B-7) አካቷል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!