ዕለተ ሰኞ ጥቅምት 23-2013 ዓ.ም ለጥቅምት 24 አጥቢያ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ሽበርተኛው ሕወሀት በክህደት ጥቃት መፈጸሙ ሁሌ የሚታወስና ፈፅሞ የማይዘነጋ እለት ነው።
እለቱን ስናስብ ለአመታት ቤት ንብረታቸውን ትተው የአገርን ዳር ድንበር እና ሉአላዊነት ለማስከበር ሐሩር እና ቁሩ ሳይበግራቸው በቀበሮ ጉድጓድ የቆዩት እና የትግራይ ሕዝብ ችግር ችግሬ ብለው ካላቸው እያካፈሉ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮቹን ከማንም ቀድመው ሲጋፈጡ የኖሩ የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ጭካኔ በአሸባሪው ህዋሃት ባልጠበቁት እና ባላሰቡት ሰዓት የተካዱና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸውን ጀግኖች ሰማዕቶቻችንን በልባችን ታትመዋልና መቼም አንረሳቸውም!
ትውልድም ሲዘክራቸው ይኖራል።
ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ እለቱን “ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል ስንዘክር ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን የተዘረጋለትን የሰላም እጅ ገፍቶ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪ ሕወሀትን ወረራ በመቀልበስና የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት እኒያ ክህደት የተፈጸመባቸውን ሰማዕታት አደራ በጀግንነት በወጣት ላይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ከፍ ብላለች!
ዛሬም በሀገር ወዳድ ልጆችዋ ሉዓላዊነትዋ መከበሩን ሰንደቅዋ ከፍ ብሎ መውለብለቡን ቀጥሏል! ጀግኖቻችንን እያመሰገንን እነሱ በደማቸው ያጸኗትን ሀገር ሌት ተቀን ሰርተን ድህነትን ተፋለመን በማሸነፍ የሀገራችንን ነጻትና ሉዓላዊነት እናጸናለን!
ውድ የከተማችን ነዋሪ በውጪ ጠላቶቻችን አዝማችነት ሀገር ለመበተን ጥቃት የፈጸሙብንን ህወሀትንና ጀሌዎቹን በጀግንነት በመመከት የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ወደር የለሽ መስዋእትነት እየከፈለ ካለው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ አንደ ሁልጊዜው ከሰራዊታችን ጎን በመቆም ደጀንነቱን እንዲያረጋግጥ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ዕለቱን ሁሉም የመንግስት፣መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ነዋሪው ሕዝብ በተመሳሳይ ሁኔታ በሚከተለው መልኩ የሚዘከር ይሆናል።
ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ለ አንድ ደቂቃ ክላክስ ያሰማሉ።
ከጠዋቱ 4:30 በተመሳሳይ ሰዓት ሁሉም በከተማችን የሚገኙ የመንግስት ና የግል ተቋማት አመራሮች ፣ ሰራተኞች እና መላው ነዋሪ በተሰማራበት እና ባለበት ቦታ በመቆም የቀኝ እጁን በግራ ደረቱ ላይ በማድረግ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ስለኢትዮጵያ የከፈላችሁትን አንረሳም” በማለት ለሰማዕታቱ ያለውን ክብር የሚገልፅ ይሆናል።
“ጥቅምት 24ን መቼም አንረሳውም”!!!
አዲስ አበባ ጥቅምት 23 ቀን 2015