አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፤ 2015 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አቅም ማጎልበትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የተቋማት አቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ የአገልጋይነት ችግሮችን ለመፍታት በአገልግሎት አሰጣጥ ስነምግባር ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ስልጠናው በዋናነት ያስፈለገበት ምክንያት የትራንስፖርት ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የአገልግሎት አሠጣጥ እና የስራ ላይ ሙያ ስነ-ምግባር ላይ ትኩረት ተሠጥቶ የዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማሻሻል የሚያሥችል አቅም እንዲኖር ለማድረግ ነው፡፡
ትራንስፖርት ዘርፉ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ህዝብ አገልግሎት ሰጪዎች ሲመጣና አገልግሎት ሲሰጥ ፍፁም ሙያዊ ስነ ምግባር ተላብሶ ለተሰማራበት ሙያዊ ስራ ክብር ሰጥቶ ማገልገል እንደሚገባና ህብረተሰቡ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ በስልጠናውም ተዳሷል፡፡
በተጨማሪም ሰልጣኞቹ አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ የስራ ተነሳሽነት እንዲኖር ሙያዊ ስነ ምግባር እንዲዳብር /እንዲሻሻል/ እና በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ህብረተሰቡ የተሻለ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት ያስችላል ሲሉ የአቅም ማጎልበትና ስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አብርሃም አድነው ገልፀዋል፡፡
በሥልጠናውም 32 የማህበራት አመራሮች እና ከ 100 በላይ ለሚሆኑ በአንበሳ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ለተሰማሩ ሴት ትኬተሮች ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም በዘርፉ በአገልግሎት ሰጪነት የተሰማሩ ባለሙያዎች ስልጠናው ለመስጠት ቢሮው መዘጋጀቱንና ስልጠናው ተከታታይነት እንዲኖረው የሚሰራ ይሆናል፡፡