(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቀደም ሲል ባፀደቀው የሞተርና የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል መመሪያ ቁጥር 155/2016 መነሻነት ለአስፈፃሚ አካላት አገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ ግልፀኝነትና የአሰራር ስርዓት ለማዘርጋት በትራንስፖርት ፕላኒንግና ስትራቴጂክ ጥናት ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ረቂቅ የአፈፃፀም ዝርዝር ማንዋል ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
በመመሪያው ስልጣንና ኃላፊነት በተሰጣቸው የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፣ የመከታተያ ስርዓት ቴክኖሎጂ (ጂፒኤስ) አቅራቢ ድርጅት፣ አገልግሎት ሰጪ ማህበራትና ባለንብረቶችም ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን፤ በማንዋሉ መካተት ያሉባቸውን ገንቢ ሀሳቦች አንስተዋል።
በመጨረሻም የትራንስፖርት ፕላኒንግና ስትራቴጂክ ጥናት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሐመድ ሁሴን በውይይቱ የተነሱ ገንቢ ሀሳቦችን በመውሰድ የአፈፃፀም ዝርዝር ረቂቅ ማንዋሉ በድጋሚ ተከልሶ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልፀዋል።