(የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የካቲት 25/2016ዓ.ም)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉ የተመረጡ ተቋማት በተደረገው አዲስ የሪፎርም አደረጃጀት መነሻነት የቢሮው ሰራተኞች ውጤታማናነትን ለማሻሻልና የአገልጋይነት መንፈስን ለማስረፅ ስልጠናው ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ተገልጿል።
ስልጠናው የሚሰጠው በሁለት ዙር ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞችን በሁለት የስልጠና ማዕከል በመክፈል ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል።
በእለቱ ስልጠናውን ያስጀመሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቁ ደስታ ለአምስት ቀናት በባህሪ ቀረፃና በተግባር ክህሎት ዙሪያ ስልጠናው እንደሚሰጥ ገልፀው፤ በስልጠናው ሪፎርሙ በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እና ተቋማት ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲየመጡ ያስችላል ብለዋል።
ስልጣኞች የባህሪ ወይም የአመላካከት ለውጥ በማምጣት ብልሹ አስራሮችንና ሌብነትን በመቀነስ እንዲሁም ቀልጠፋና ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው አሰልጣኞች ገልፀዋል።
ቴሌግራም ቻናል:-https://t.me/transport_bureauhttps://
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!