፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፐብሊክ ሰርቨስ ቢሮ፤ መጋቢት 9 ቀን 2016ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃለፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በከተማው በተመረጡ 16 ተቋማት ሲከናወን የነበረው የሪፎርም ስራ ተጠናቆ ወደ ትግበራ ምዕራፍ መገባቱን በማስመልከት ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥተዋል።
የተገልጋዩን ህብረተሰብ ክፍል እርካታ ለመጨመር እንዲቻል በተመረጡ 16ቱም ተቋማት ሲከናወን የነበረው የሪፎርም ስራ ዓላማ ተገቢውን ብቃት አሟልተው ለያዙ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት መስጠት ፤የተቋማትን መዋቅር ለመከለስና ብልሹ አሰራርን በዘላቂነት ለማስቀረት ትኩረት ያደረገ መሆኑን የቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በመግለጫቸው ወቅት ይፋ አድርገዋል ።
ከሪፎርም የሚጠበቀው ወጤት በከተማዋ በዘላቂነት የተቋም ግንባታ እውን እንዲሆን ማስቻል መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው ሲከናወን የነበረው አጠቃላይ የሪፎርም ስራ ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ አሰራሮችን ማዕከል ያደረገ መሆኑን አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል ።
አዲሱ የሪፎርም አዋጅ 84/2016 ፀድቆ ተግባራዊ መደረጉን አያይዘው የጠቀሱት ኃላፊው በከተማ ደረጃ 60 % የሪፎርም ሂደቶችን አሟልተው ያለፉ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት የሚሰጣቸው ሲሆን ፤ቀሪዎቹ በክፍለ ከተማና ወረዳ የሰው ኃይል ክፍተት በሚስተዋልባቸው ስፍራዎች ተመድበው አገልግሎት ይሰጣሉም ተብሏል ።
በሪፎርም ሂደት ባለፉ የተመረጡ 16ቱም ተቋማት 42 የአይሲቲ መሰረተ -ልማት ዝርጋታ ስራ ተጠናቆ በአጭር ግዜ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑም በኃላፊው መግለጫ የተካተተ ሲሆን፤ከ19ሺህ በላይ በተቋማቱ የሚያገለግሉ የመንግሥት ሰራተኞች በሁለት ዙሮች የሪፎርም ስራዎች አካል የነበረውን ፈተና የወሰዱ መሆናቸው ተረጋግጧል ።
እንደ ኃላፊው ቀጣይ ማብራሪያ ፈተናውን ከወሰዱት መካከል 33 ፐርሰንት የሚሆኑ ዳይሬክተሮችና የቡድን መሪዎች የስራ ስምሪት ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፤50.6 ፈተናውን ያለፉ ባለሙያዎች በሚመጥናቸው መደብ ላይ ድልድል የተደረገላቸው መሆኑ ተጠቁሟል ።
ፈተናውን ማለፍ ያልቻሉ ባለሙያዎች ሁለት ደረጃ ዝቅ ተደርገው እንዲመደቡ በሚፈቅደው መመሪያ መሰረት መስተናገዳቸውን ያሳወቁት ዶ/ር ጣሰው፤ከፈተናም በኋላ ከ17ሺህ በላይ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች የባህሪና የቴክኒክ ብቃት ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን አስረድተዋል ።
በከተማ አስተዳሩ ለሚተገበረው የሪፎርም ስራ ውጤታማነት አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በድስፒልን መወጣት እንደሚኖርበት በአንክሮ አሳስበዋል ።