ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሰሞኑ የኮሪደር ልማቱን አስመልክተው ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ፦
ከምትክ ቦታ ጋር በተያያዘ ሰፊ ቦታ ያስፈልገናል ያሉትን በኮልፌ ቀራንዮ፣ ጉለሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ቦታዎች ተሰጥቷቸዋል፡፡
በከተማዋ መሀል አካባቢዎች መቆየት ነው የምንፈልገው ያሉትን ቂርቆስ፣ልደታና አዲስ ከተማን የመሳሰሉ መሀል ከተሞች ላይ ባሉ ኪስ ቦታዎች እንዲስተናገዱ ተደርጓል ፡፡
ከቀበሌና ከኪራይ ቤት ውጪ ያሉ ቤቶች ከመኖሪያ ቤት ግንባታቸውን እስከሚፈጽሙ የአንድ አመት የቤት ኪራይና የማጓጓዣ ክፍያ ተፈፅሟል ፡፡
የቀበሌ ቤቶችንና የኪራይ ቤቶችን ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችም ተደራጅተው የንግድ ስራቸውን ሊያስቀጥልላቸው በሚችል አካባቢ ቋሚ መስሪያ ቦታ እንዲያገኙና ባለይዞታ እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡
ከመንገድ ወደ ውስጥ ሆነው የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ የነበሩ ወደ 551 ለሚሆኑ ሰዎችም አሁን ከሚሰሩበት የተሻለና ሰፋ ያለ የመስሪያ ሼድ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ፡፡
አራዳ ክፍለ ከተማ አካባቢ ብቻ 1ሺህ 400 የሚደርሱ ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤት መርጠው ቋሚ የቤት ባለቤት በመሆን የተሻለ ህይወት መምራት ችለዋል ፡፡
መክፈል አንችልም በኪራይ ቤት ነው የምንቀጥለው ያሉ 402 ነዋሪዎችም አቃቂ አካባቢ ከተገነቡ ተገጣጣሚ ቤቶች ውስጥ እጅግ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሏል፡