አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2012፤ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች በአዲስ አበባ የትራንስፖርት መጨናነቅን በመቀነስ የኮረናቫይረስን ለመከላከል ለቀረበላቸው ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ መስጠት ጀምረዋል።
በዚሁ መሰረት ጎልደን ባስ ትራንስፖርት እና የኛ ባስ አክሲዬን ማህበር እያንዳንዳቸው አስር አውቶቡሶች መድበው ወደ ስራ ገብተዋል።
በዚህም ህብረተሰቡ በትራንስፖርት እጥረት እንዳይጉላላ የበኩላቸውን አስተዋጾ እያደረጉ ይገኛሉ ብሏል።
ተቋማቱ ለሀገራዊ ጥሪው ለሰጡት ምላሽ ምስጋና እያቀረበ ሌሎችም የትራንስፖርት ሰጪ ተቋማትም የከተማዋን ትራንስፖርት ለመቅረፍ ርብርብ መደረግ እንዳለበት ማሳሰብ እንወዳለን።