( የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ነሐሴ 25/2016ዓ.ም) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል እንዲሁም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል።
ቢሮው አሁን ያለውን የህዝብ ትራንስፖርት የባለሶስት እግር ወይም ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን የሕግ ጥሰቶችንና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል እና አገልግሎት አሰጣጡን ለመቆጣጠር እንዲያስችል ከዚህ ቀደም በህጋዊ ማህበር በመደራጀት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ባለንብረቶች ተሽከርካሪው ከነበረበት ክልል ክሊራንስና የአዲስ አበባ ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ በማቅረብ ምትክ የአዲስ አበባ ሰሌዳ ማውጣት እንደሚገባ ቢሮው ያሳውቃል።
ይህንን አሟልተው እስኪገኙ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ከነገ ነሐሴ 26/2016ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ቢሮው በጥብቅ እያሳሰበ፤ ወደ አገልግሎት ለመመለስ ቀደም ሲል አገልግሎቱን ሲሰጡበት ከነበረው የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስፈላጊውን ህጋዊ መረጃ በማሟላት ቢሮው በሚያስቀምጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት አገልግሎቱን መስጠት እንሚቻል ቢሮው አሳውቋል።
ይህንን ተላልፈው በሚገኙ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች በቢሮውና በሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለተጨማሪ መረጃ
ድረ ገጽ፦ https://www.aatb.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/aatb
ለበለጠ መረጃ፡- 011-666-33-74 ወይም
ነፃ የስልክ መስመር 9417 ይጠቀሙ!