በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅ/ጽ/ቤቶች: የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጠ::

*************

(ት/ማ/ባ ነሃሴ 18//2016 ዓ,ም)

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ቅ/ጽ/ቤቶች: የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል::

በስራ አፈጻጸማቸው ከ1_3 ደረጃን ያገኙት ቅ/ጽ/ቤቶች ልደታ:ለሚኩራ እና ቦሌ ሲሆኑ ከማእከል ዓላማ ፈጻሚ ዳይሬክቶሬቶች መካከል የቄጥጥርና ደንብ ; የመንገድ ደህንነት ምህንድስና እንዲሁም የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ዳይሬክቶሬቶች በደረጃ ከ1_3 ተቀምጠዋል::

በውጤት ደረጃቸውም መሠረት ኮምፒውተር: ዋንጫና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል::

ከደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች መካከል 1ኛ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች: ዳይሬክቶሬት: 2ኛ የአገልግሎት አሰጣጥ: የክትትል: ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት 3ኛ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት በየደረጃቸው የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል::

በተጨማሪም በማእከልና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከ1_3 ደረጃን የያዙ ባለሙያዎቾ የእጅ ሰዓትና ሰርተፊኬት ተሸልመዋል::

እንዲሁም ተቌሙን በሙያቸው ለደገፉ አርቲስቶች እውቅና ተሰጥቷል::

Leave a Reply