በአዲስ አበባ ከተማ በቀን እስከ 80 ሺ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ እንዲችል ተደርጎ ከፍ ባለ የጥራት ደረጃ እየተገነባ የሚገኘው የኤምፔሪያል ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በቅርቡ ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በአሁኑ ወቅት የማሳለጫ ድልድዩ የመቃረቢያ መንገዶች እና ቀሪ የግንባታ ቦታዎች ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን አጠቃላይ የፊዚካል አፈፃፀሙም 82 በመቶ ደርሷል፡፡
በቀጣይ ጥቂት ቀናት ውስጥ ከመንገድ ዳር መብራት ተከላ እና ከእግረኛ መንገድ ስራዎች ውጪ የአስፋልት ማንጠፍ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅም ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ከማሳለጫ ድልድዩ በተጨማሪ የመቃረቢያ መንገዶቹን ጨምሮ አጠቃላይ 1.8 ኪ.ሜ ርዝመትና 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ለግንባታ ወጪውም ከ714.8 ሚሊዮን ብር በላይ ተይዞለታል፡፡
ዘገባው፦ኢፕድ ነው