በሙያዊ ስነምግባር ማገልገል ለአገልግሎት አሰጣጡ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የአቃቂ ቃሊቲ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ገለፀ።

(አዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፤ ሰኔ 07/2016) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዛሬ ለባለድርሻ አካላት በአመራር ክህሎትና በአገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ዘውዴ ቢሮው ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ አገልግሎቱን ለማሻሻል በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት የሚሰጡትን አገልግሎት በሙያዊ ስነምግባር መስጠት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖር ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ተሾመ እና የሥነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት ጥበቡ በአመራር ከህሎት ላይ እና በሙያዊ ስነምግባር ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል።

በስልጠናውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ተገልፀዋል።

በተጨማሪም የማህበራት አመራሮች በስራቸው ያሉ አባላትን የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በመፍጠር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተጠቁሟል።

በስልጠናውም የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሰራተኞች፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረት ማህበራት አመራሮች፣ የታክሲ ተራ ማስከበር ማህበራት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ለተጨማሪ መረጃ

!

Leave a Reply