አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7፣ 2012፤ በአዲስ አበባ ከተማ የኩላሊት ህመምተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከ5 ሺህ በላይ ታክሲዎች ለህመምተኞቹ ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለፀ።
የነጻ የትራስፖርት አገልግሎቱን መስጠት የጀመሩትም ዘሉሲ ሜትር ታክሲና ሰማያዊ በነጭ ታክሲዎች ማህበር አባላት ናቸው።
ዘሉሲ ሜትር ታክሲና ሰማያዊ በነጭ ታክሲዎች ማህበር አባላት ለኩላሊት ህመምተኞች ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት ያመቻቹት ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስና ያለባቸውን የወጪ ጫና ለማቃለል ታሰቦ እንደሆነ ተገልጿል።
የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ እስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ህመምተኞች ከሌሎች ግለሰቦች ጋር በህዝብ ትራስፖርት ቢጠቀሙ ለቫይሰሩ የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ታክሲዎች ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል።